በፈረንሳይ እና በUK ውስጥ ለጥገኝነት ጠያቂዎች የሥራና የገንዘብ አበል ክፍያ ንጽጽር 

ጥገኝነት ጠያቂ እንደመሆኔ መጠን ሥራ መሥራት ሕጋዊ ነው?  

FRANCE (ፈረንሳይ)

ለመጀመሪያዎቹ አስራ ሁለት ወሮች መስራት አይፈቅድም:: ጥገኝነት ጠያቂዎች ሥራ እንዲሰሩ አይፈቀድላቸውም:: ህገ-ወጥም ነው::  በህገ ወጥ መንገድ ሲሰሩ ከተያዙ እስር ቤት ሊገቡ ይችላሉ::  

 

የጥገኝነት ማመልከቻዎን በተመለከተ ከፈረንሳይ መንግስት በሰድስት ወር ውስጥ መልስ ካልተሰጠው መስራት ይፈቀድልዎታል::  

ይሁን እንጂ በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ የሥራ ስምሪት ማግኘት አስቸጋሪ ነው:: the Collectif de soutien des exiles du 10ème arrondissement de Paris. ምክርን ጠይቁ:: (ምንጭ - French Refugee Council) 
 
ይሁን እንጂ ጥገኝነት ጠያቂዎች በህጋዊ መንገድ ሥራ ሊሰሩባቸው በሚችሉት የሙያ ዝርዝር ውስጥ አንዳንድ ሙያዎች አሉ:: እነዚህም የኮምፒተር ሳይንቲስቶችን ወይም የግንባታ ቦታ አስተዳዳሪዎች ያካትታል:: አስፈላጊ ዝርዝሮች እርስዎ በሚገኙበት ክልል መሠረት ይለያያሉ:: ሙሉ ዝርዝሮች እዚህ ይገኛሉ:

https://www.legifrance.gouv.fr/affichTexte.do?cidTexte=JORFTEXT000017937372 

UNITED KINGDOM 

 

ለመጀመሪያዎቹ አስራ ሁለት ወሮች መስራት አይፈቅድም:: ጥገኝነት ጠያቂዎች ሥራ እንዲሰሩ አይፈቀድላቸውም:: ህገ-ወጥም ነው::  በህገ ወጥ መንገድ ሲሰሩ ከተያዙ እስር ቤት ሊገቡ ይችላሉ:: 
 
 
ይሁን እንጂ ጥገኝነት ጠያቂዎች በህጋዊ መንገድ ሥራ ሊሰሩባቸው በሚችሉት የሙያ ዝርዝር ውስጥ አንዳንድ ሙያዎች አሉ:: እነዚህም ነርሶች፣ ዘመናዊ ዳንስኞቸ እንዲሁም የጂኦፊዚክስ ባለሙያዎችን ያጠቃልላል:: .  

የስደተኝነት የመኖሪያ ፍቃድ ካገኘሁ ሥራ መሥራት ቸላለው?

FRANCE (ፈረንሳይ)

አዎ የስደተኛነት  የመኖሪያ ፍቃድ ካገኙ በፈረንሳይ ውስጥ የመሥራት መብት አለዎት::   

UNITED KINGDOM 

አዎ እንደ እንግሊዝ ዜጎች ለመሥራት ተመሳሳይ መብት አለዎት:: 

በጥገኝነት ጠያቂነት ምን አይነት የገንዘብ እርዳታ አገኛለሁ? 

FRANCE (ፈረንሳይ)

የክፍያው መጠን በስቴቱ የመኖሪያ ቤት ተሰቷቿል ወይም አይደለም የሚለው ላይ ነው የሚመሰረተው::  ነገር ግን ይህ ደንብ ዋስትና አይሰጥዎትም::  
 
በመጠለያ ማእከል ውስጥ ከሆኑ በቀን €6.80 ያገኛሉ::   
 
በመጠለያ ማእከል ውስጥ ካልሆኑ ኢራስዎ ለመኖርያ ቤት እንደሚከፍሉ ይጠበቃል ለዚህም በቀን €14.20 ያገኛሉ:: ተጨማሪ €7.40 ለግል መኖሪያ ቤት ለመክፈል አስቸጋሪ ነው ለዚህም ብዙ ጥገኝነት ጠያቂዎች በመጥፎ  ሁኔታ ውስጥ ይኖራሉ::  (ምንጭ -Asylum in Europe).

 

UNITED KINGDOM 

ሁሉም ጥገኝነት ጠያቂዎች በቅድሚያ ጥያቄዎቻቸው በሳምንት £ 37.75 የማግኘት መብት አላቸው:: ይህ ዓይነቱ የገንዘብ ድጋፍ ሴክሽን 96 ተብሎ ይጠራል:: ብዙውን ጊዜ ከአንዳንድ የገንዘብ ማሽኖች ገንዘብዎን በሚከፍሉበት የዴቢት ካርድ (Aspen ካርድ ይባላል) ይቀርባል:: የጥገኝነት ጠያቂዎች በየወሩ በመደበኛነት ፖስታ ቤት በመሄድ መፈረም አለባቸው::  ይህ ሲቀየር ይነገርዎታል::  
 
ጥገኝነት ጠያቂዎች የመጀመሪያ ጥያቄዎ ውድቅ ከተደረገ የእነሱን የገንዘብ ድጋፍ ዓይነት መለወጥ አለባቸው:: ይህ ዓይነቱ ክፍል 4 በመባል ይታወቃል:: በሱቁ ውስጥ አንዳንድ ሸቀጦችን ለመግዛት በካርድ ላይ £35.39 ይቀበላሉ:: ጥገኝነት ጠያቂዎች ሁለተኛ ጥያቄያቸውን / አዲስ ጥያቄን በመጠባበቅ ላይ ሆነው አሁንም ድረስ እንዲስተናገዱ ይደረጋል:: 

This page is run by the UK registered charity, Refugee Info Bus - for more info on our work, check out our website. 

PO BOX:  Po Box 28652, Edinburgh, EH4 9EX

Registered UK Charity Number: 1168538

  • Facebook
  • Twitter
  • Instagram