ፖሊስ የምን ሰነድ ነው የሰጠኝ?

ከፖሊስ ሊቀበሉ የሚችሏቸው 2 ዋና የሰነዶች ዓይነቶች አሉ፥

 

  1.  የ “Procès Verbal” እና/ወይም

  2. “Obligation de Quitter le Territoire Français” (OQTF)

 

 “Procès Verbal” ምንድን ነው?

“procès verbal” የተከናወኑ ክስተቶችን የሚመዘግብ በፖሊስ የተጻፈ ሰነድ ነው፡፡ የማስጠንቀቂያ ቃል በሁለት መንገድ ይሰጣል 

 

(1)ለማንነት ምርመራ በፖሊስ ቁጥጥር ስር በሚውሉበት ጊዜ ወይም (2) ሲታሰሩ (“garde à vue” ውስጥ ከተቀመጡ) ምክንያቱም ፖሊስ ወንጀል ፈጽመዋል ወይም ወንጀል ለመፈፀም ሞክረዋል በለው ስላሰበ።

“procès verbal” ካለዎት ፖሊሶች እንደገና እንዳያያዙ አያግድዎትም   (ምንም እንኳን በተግባር በካሊስ እና ደንኪክ ውስጥ እርስዎ ቀድሞውኑ ታስሮው ከሆነ  እንኳን እንደገና አያዙዎትም) 

 

የ Procès Verbal ን ከተቀበሉ ምን ማድረግ ይጠበቅብዎታል?

የተቀበሉትን ማንኛውንም ‹Procès Verbal› ን እንዲፈርሙ ይጠየቃሉ ፣ ነገር ግን ‹Procès Verbal› ን መፈረም የለብዎትም፡፡ እነሱ ባወጧቸው ሁሉም እውነታዎች እስካልተስማሙ ድረስ “procès verbal” መፈረም የለብዎትም ምክንያቱም ይህ በተሳሳተ የክስተት ስብስብ እንዲስማሙ ያደርግዎታል፡፡ 

ሆኖም ፣ ካልፈረሙትም  ይመዘገባል። 

የ “proces verbal” ከ “Obligation de Quitter le Territoire Français” (OQTF) ጋር ተያይዞ ሊቀበሉ ይችላሉ። የተቀበሉትን “proces verbal” የፈረንሳይን ክልል ለቀው እንዲወጡ የሚጠይቅ ሰነድ የሚከተል መሆኑን ያረጋግጡ፡፡

 

OQTF ምንድን ነው?

 

“Obligation de Quitter le Territoire Français” ጥሬ ትርጉሙ ከፈረንሳይ ሀገር ለቆ የመወጣት ግዴታ ነው።ስደተኞቹን ከፈረንሳይ ለማስወጣት ስራ ላይ የዋለው ዋናው ሰነድ ሲሆን ከፈረንሳይ እንዲወጡ ይጠይቃል፡፡ ይህ ብዙውን ጊዜ በፈረንሣይ ውስጥ የመኖር መብትዎን የሚያረጋግጥ ወረቀት ከሌለዎት እና የጥገኝነት ጥያቄዎ ውድቅ ተደርጓ ከሆነ ወይም የመኖሪያ ፈቃድዎ ጊዜው ካለፈ ነው። OQTF የሚሰጠው ብዙውን ጊዜ በማንነት ምርመራ ውጤት ወቀት ነው  ፣ እርስዎን ለመለየት እና ፈረንሳይ ውስጥ የመሆን መብት እንዳለዎት ለማወቅ የጣት አሻራዎችዎ ይወሰዳሉ፡፡

በተለምዶ OQTF ሳይዘገዩ ወዲያውኑ እንዲወጡ ያዛል ፣ ይህ ማለት ከፈረንሳይ ለመውጣት 48 ሰዓታት አለዎት ማለት ነው ፡፡ በተጠየቀው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካልለቀቁ በቁጥጥር ስር ሊውሉ ወይም በቤትህ በቁጥጥር ስር ሊቆዩ ይችላሉ፡፡ ይህም የምሆነው ትዕዛዙ ከተቀበሉ በኋላ እስከ አንድ ዓመት ወስጥ ነው።

 

 OQTF ከተቀበሉ ምን ማድረግ ይኖርብዎታል?

አብዛኛዎቹን OQTF ን ለመቃወም 48 ሰዓታት ብቻ ነው ያለዎት።. ስለሆነም በተቻለ ፍጥነት የሕግ ምክር መፈለግ አለብዎት፦

በካለ (Calais) ውስጥ ከሆኑ ለ  La Cabine/Legal Shelter  እንዲያመለክቱ ፈቃደኛ ሠራተኛ ይጠይቁ፡፡

ዱከርክ (Dunkerque)l ለ La Cimade እንዲያመለክቱ ፈቃደኛ ሠራተኛ ይጠይቁ፡፡

ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ከሆነ እና OQTF ተሰጥቶት ከሆነ ፈቃደኛ ሠራተኛ ለRefugee Youth Service እንዲያመለክቱ ይጠይቁ፡፡

This page is run by the UK registered charity, Refugee Info Bus - for more info on our work, check out our website. 

PO BOX:  Po Box 28652, Edinburgh, EH4 9EX

Registered UK Charity Number: 1168538

  • Facebook
  • Twitter
  • Instagram