በUK ውስጥ ጥገኝነት ለመጠየቅ ተግባራዊ መረጃ

የጥገኝነት ጥያቄዎ በሂደት ላይ እያለ መኖሪያ (ማረፊያ)

 1. የጥገኝነት ጥያቄ መመዝገብ 

 

  2. የማጣሪያ ቃለ መጠይቅ ፣ 'ችግር ውሰጥ መሆኖን'መገምገም


 

  3. ችግር ውሰጥ ከሆኑ ‹የመጀመሪያ መጠለያ› ውስጥ መመደብ 



  4. ለድጋፍ ማመልከት 



  5. ቋሚ በሆነ ሌላ መኖሪያ እና የገንዘብ ድጋፍ 


 

  6. የጥገኝነት ጥያቄ ላይ ውሳኔ

የመጀመሪያ መኖሪያ ቤት 

 • የጥገኝነት ጥያቄ በተመዘገበበት ጊዜ የአጭር ጊዜ መኖሪያ ቤት

 • በአጠቃላይ ከ3-4 ሳምንታት

 • ሆስቴል - ብዙውን ጊዜ የጋራ ክፍሎች

 • ሙሉ እገዛ ፣ ግማሽ እገዛ ወይም ራስን መመገብ

 ቋሚ የሆነ ሌላ መኖሪያ

 • የጥገኝነት ጥያቄዎ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ እስከሚሰጥበት ድረስ የሚቆዩበት የረጅም ጊዜ መጠለያ

ጥገኝነት ፈላጊዎች የተወሰኑ መስፈርቶችን ካሟሉ የመጠለያ እና የገንዘብ ድጋፍ የማግኘት መብት አላቸው ፡፡  መመዘኛዎች:

 • የጥገኝነት ጥያቄው በሂደት ላይ ከሆነ

 • 'ችግር ውሰጥ የመሆን ግምገማ’ ካለፉ፦ ለራስዎ እና ለቤተሰቦዎ የኑሮ ወጪዎችን ለመሸፈን የሚያስችል በቂ ገንዘብ  ወይም በቂ መኖሪያ እንደሌለዎት ካሳዩ

 • የጥገኝነት ጥያቄዎን በተቻለ ፍጥነት ተቀባይነት ባለው ጊዜ መጠየቅ  (ብዙውን ጊዜ ወደ UK በገቡበት ቦታ ወይም ከገቡ በሦስት ቀናት ውስጥ)

የመጠለያ እና የገንዘብ ድጋፍ እንቀጥል ማሟላት ያለብዎት ሁኔታዎች፦

 

 • የጉዞ ዝግጅቶችን ይከተሉ (ለምሳሌ ፣ መኖሪያን እንዲያዛወሩ ሊጠየቁ ይችላሉ)

 • በተፈቀደ አድራሻ መኖር

 • የመኖርያ ደንቦችን መከተል 

 • በኢሚግሬሽን መኮንን የተቀመጠውን ሪፖርት የማድረግ መስፈርቶችን ማሟላት

 • የ Home Office ጥያቄዎችን ያሟሉ (ለምሳሌ፡ የጥገኝነት ቃለመጠይቆች ላይ መገኘት ወይም በጥገኝነት ጥያቄዎ ላይ መረጃ መስጠት)

 

መጠለያ (መኖሪያ ቤት)

 

ጊዜያዊ እና መሰናዶ መጠለያዎች ያለ ምርጫ ይሰጣሉ። ይህ ማለት እርስዎ የሚኖሩበትን ቦታ መምረጥ 

አይችሉም፡፡

 

ቤተሰቦች በተለምዶ በራሳቸው የሚገለገልበት ወጥ ቤት እና መታጠቢያ ያላቸው ቤት ይሰጣቸዋል፡፡

 

ነጠላ ሰዎች ፣ ልጆች የሌሏቸው ባለትዳሮች እና ነጠላ ወላጆች በተለምዶ መኖርያ ቤት ይጋራሉ። እያንዳንዱ ቤት ማእድ ቤት ፣ የመታጠቢያ ክፍል ፣ የመመገቢያ ጠረጴዛ እና ወንበሮች ፣ የመታጠቢያ መገልገያዎች እና የህፃናት መንከባከቢያ መሳሪያዎች አቅርቦት ይኖረዋል። እንደደረሱ ፎጣዎች እና የአልጋ ልብስ ይሰጥዎታል፡፡

 

በመጠለያው ውስጥ ጋዝ ፣ ውሃ እና ኤሌክትሪክ ይካተታሉ። ምንም ክፍያ የለም።

 

የገንዘብ ድጋፍ (ሴክሽን 95 ድጋፍ)

 

ለጥገኝነት ፈላጊዎች የገንዘብ ድጋፍ ክፍያዎች ለእያንዳንዱ የቤተሰብ አባል በሳምንት £ 37.75 ነው።   ገንዘቡ ብዙውን ጊዜ በየሳምንቱ Home Office በዴቢት ካርድ (ASPEN ካርድ በሚባለው) ይገባል። ካርዱ በአብዛኛዎቹ ሱቆች ውስጥ ለመክፈል ወይም ገንዘብን ለማውጣት ያገለግላል።

 

ተጨማሪ ድጋፍ መጠየቅ የሚችሉበት አንዳንድ ሁኔታዎች አሉ፦

 • ነፍሰ ጡር ከሆኑ በሳምንት ተጨማሪ £ 3 ማግኘት ይችላሉ

 • ነፍሰ ጡር ከሆኑ ደግሞ የአንድ ግዜ ክፍያ £ 300 መጠየቅ ይችላሉ ፡፡ ከመወለዱ ቀን በፊት ባሉት ስምንት ሳምንታት መካከል እና ከወለዱ በኋላ እስከ ስድስት ሳምንታት ድረስ ማመልከት አለብዎት፡፡ እንዲሁም ልጅዎ ከ UK ሀገር ውጭ የተወለደ እና ከሶስት ወር በታች ከሆነ £ 300 መጠየቅ ይችላሉ

 • በእርግዝና ወቅት ተጨማሪ ክፍያን ለመጠየቅ ለ Home Office ደብዳቤ ከአዋላጅ ወይም ከ GP ወይም ከ MAT B1 የወሊድ የምስክር ወረቀት ግልባጭ (ከአዋላጅ ወይም ከ GP የሚገኝ) ይላኩ፡፡

 • ከአንድ አመት እድሜ በታች ላሉት ለእያንዳንዱ ልጆች በሳምንት ተጨማሪ £ 5 መጠየቅ ይችላሉ

 • ከአንድ እስከ ሶስት ዓመት እድሜ ላለው ልጅ በሳምንት ተጨማሪ £ 3 መጠየቅ ይችላሉ

 • ለልጆች ተጨማሪ ክፍያን ለመጠየቅ ለ Home Office ኦሪጂናል የልደት የምስክር ወረቀት ወይም ሌላ የልደት ቀን የሚያረጋግጥ መደበኛ ማስረጃ መላክ አለብዎት 

 

ተደጋግሞ የሚነሱ ጥያቄዎች

 

ጥ: የምኖርበትን ቦታ መምረጥ እችላለሁ?

መ: አይ። ቦታውን መምረጥ አይችሉም ፡፡ ልዩ መስፈርቶች (እንደ አካል ጉዳተኝነት ያሉ) ግምት ውስጥ ይገባሉ፡፡

 

ጥ: ለቤተሰብ አባላት ድጋፍ መጠየቅ እችላለሁ?

መ: አዎ። የሚከተሉትን መጠየቅ ይችላሉ-

 • ጥገኞች (የትዳር ጓደኛ እና ዕድሜያቸው ከ 18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች)

 • ቢያንስ ለ 6 ወራት ያህል ከቤተሰብዎ ጋር አብረው የኖሩ ከ 18 ዓመት በታች የሆኑ ሌሎች የቅርብ የቤተሰብ አባላት

 • የአካል ጉዳት ያለባቸው ከ 18 ዓመት በላይ የሆኑ አዋቂዎች

 

ጥ: ሌሎች ጥቅሞችን እንዲሁም የድጋፍ ክፍያን መጠየቅ እችላለሁን?

መ: አይ። ጥገኝነት ፈላጊዎች በአጠቃላይ ለሌሎች ጥቅሞች ብቁ አይደሉም ፡፡

ጥ: ነፃ የጤና እንክብካቤ ማግኘት እችላለሁን?

መ: አዎ። ጉዳያቸው እየታየ ያሉ የጥገኝነት ፈላጊዎች እና ወይም ይግባኝ ያላቸው አመልካቾች የመጀመሪያ እና ሁለተኛ የNHS አገልግሎቶች ያለ ክፍያ ያገኛሉ። እንደ ጊዜያዊ ህመምተኛ መመዝገብ ሊኖርብዎ ይችላል። የጥገኝነት ጥያቄዎ (እና ይግባኝ) ተቀባይነት ካላገኘ ነፃ 

 ሕክምና የማግኘት መብትዎ አስቸኳይ ከሆነ ብቻ ነው፡፡

 

ጥ: ነፃ የወሊድ እንክብካቤ ማግኘት እችላለሁን?

መ: አዎ። ጥገኝነት ፈላጊዎች በብሔራዊ የጤና አገልግሎት (NHS) ላይ ሁልጊዜ የወሊድ አገልግሎት የማግኘት መብት አላቸው ፡፡ ይህም ልሆን የሚችለው።

 • ጥገኝነት ጠይቀው ውሳኔ እየጠበቁ ከሆነ 

 • የስደተኛነት ፍቃድ ተሰጥቶት ከሆነ 

የጥገኝነት የገንዘብ ድጋፍ እያገኙ ነው

ጥ: ሥራ ማግኘት እችላለሁን?

መ: አዎ።ጥገኝነት ፈላጊዎች ሥራ መሥራት የሚችሉት ያለ እነሱ ጥፋት ከ አንድ አመት በላይ ውሳኔን እየጠበቁ ከነበረ ብቻ ነው። ከዚያ የሥራ ፈቃድ ለማግኘት ለUK ድንበር ኤጄንሲ ማመልከት ይችላሉ፡፡

 

ጥ: መኖሪያ ቤት የማልፈልግ ከሆነ የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት እችላለሁን?

መ: አዎ። ችግር ውሰጥ የመሆን ግምገማ ካሟሉ ነገር ግን የሚቆዩበት ቦታ ካለዎት ለገንዘብ ድጋፍ ብቻ ማመልከት የሚችሉት፡፡

 

ጥ: በጥገኝነት ማመልከቻዬ ላይ ውሳኔ ባገኘሁ ጊዜ ምን ይሆናል?

መ: ጥያቄዎ ውድቅ ከተደረገ ከUK ለቀው ለመውጣት ዝግጅት ማድረግ አለብዎት። የድጋፍ መብትዎ ውሳኔው ከተሰጠ ከ 21 ቀናት በኋላ ያበቃል፡፡ ሆኖም በቤተሰብ ውሰጥ ልጆች ካሉ የጥገኝነት ድጋፍ ይቀጥላል። ቤተሰቡ በፍቃደኝነት አገሩን ለቅቆ መውጣት ካልቻለ ሊቆም ይችላል።

 

ጥያቄዎ ውድቅ ከሆነ ይግባኝ ማለት ይችላሉ፡፡ ይግባኙ እስከሚወሰን ድረስ የገንዘብ ድጋፍ እና የነፃ መጠለያ ማግኘትዎን ይቀጥላሉ።

 

ጥያቄዎ የተሳካ ከሆነ የጥገኝነት ድጋፍዎ ፈቃድ ከሰጥዎት ከ 28 ቀናት በኋላ ያበቃል፡፡ ከዚያ ሥራ ማግኘት ፣ ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞችን መጠየቅ እና የግል ቤት መፈለግ ይችላሉ፡፡

This page is run by the UK registered charity, Refugee Info Bus - for more info on our work, check out our website. 

PO BOX:  Po Box 28652, Edinburgh, EH4 9EX

Registered UK Charity Number: 1168538

 • Facebook
 • Twitter
 • Instagram