ከጭነት መኪና ውሰጥ ወረድኩ፤ ምን ማድረግ ይጠበቅብኛል? 

ፓስፖርት ወይም ህጋዊ የመጓጓዣ ሰነዶች ከለሌዎት የዜግነት መብት ለማግኘት ያሎት አማራጭ ጥገኝነት መጠየቅ ነው:: በተቻለ ፍጥነት ጥገኝነት መጠየቅ ለእርሶዎ ጠቃሚ ነው:: 

መጀመሪያ ላይ እርስዎን የሚወከል የሕግ አማካሪ ለማግኘት መሞከሩ ጥሩ ቢሆንም ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ በተቻለ ፍጥነት ጥገኝነት መጠየቅ ነው::ጥገኝነት ፈሊገው ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ከመጡ ብዙም ሳይቆይ ካመለከቱ ጥሩ ነው:: በጥገኝነት ጥያቄዎ ላይ ተፅእኖ ሊያመጣ የሚችለው ከቆዩ ነው:: Home Office UK ከደረሱበት ጊዜ ጀምሮ የት እንደ ነበሩ ማወቅ ይፈልጋሉ:: 

ከጭነት መኪና ውስጥ ሲወጡ፤ በዩኬ ውስጥ የት እንዳሉ ለማወቅ ይሞክሩ:: በስልክዎ ላይ ያለውን ካርታ በመመልከት ወይም አቅራቢያዎ የሚገኝ አንድ ሰው በመጠየቅ ይህንን ማድረግይችላ፤ እርስዎ የት እንዳሉ ሰው ከጠየቁ ለፖሊስ ሊያሳውቁ ይችላሉ:: 

እንዲህ ማለት ይችላሉ፡ 

“Excuse me. I don’t know where I am. Please could you tell me what area we are in?” 

የጥገኝነት ጥያቄ ለማቅረብ፤ በለንደን Croydon ለ Home Office Screening Unit ስልክ መደወል አለብዎት:: ሊልከ ቁጥሩ 020 8196 4524 ነው:: ዋጋው በደቂቃ ከ3-55p ነው:: እዚያ የማጣሪያ ቃለ መጠይቅ ይደረግለታል:: 

Croydon የማጣሪያ ክፍል መጀመሪያ ወደ ፖሊስ ጣብያ እንድትሄድ ሊነግርህ ይችላል፤በአቅራቢያዎ ያለ የፖሊስ ጣቢያ ለማግኘት ይችላሉ https://www.met.police.uk/contact/af/contact-us/find-a-police-station/ ወይም አቅራቢያዎ የሚገኝ አንድ ሰው መጠየቅ ይችላሉ:: 

እንዲህ ማለት ይችላሉ፡ 

“Hello. Where is the nearest police station?” 

ፓሊሶች ወደ ፖሊስ ጣቢያው ሊወሰዶ ሊወሰዱ ይችላሉ:: ከዚያም ማጣራ ቃለ መጠይቅ ለማድረግ ፖሊስ ወደ Croydon የማጣሪያ ክፍል ይልክዎታል:: 

የምርመራ ቃለ መጠይቅ 

ቃለ-መጠይቁ እስከ አራት ሰአት ሊወስድ ይችላል:: Right to Remain በምርመራ ቃለ መጠይቅ ላይ ምን እንደሚያደርግ ጥሩ ምክር ይሰጣል https://righttoremain.org.uk/toolkit/screening/ በተለያየ ቋንቋ ይገኛል. በዚህ የማጣቀሻ ቃለ-መጠይቅ እና ከሆም ኦፊስ (Home Office) ጋር ወደ ፊት የሚያረጉት ውይይት ተመሳሳይ መሆን አለበት:: 

ከHome Office የመጣ ጠያቂ በቃለ-መጠይቁ ወቅት በምርመራ ቃለ መጠይቅ ላይ ማስታወሻ ይይዛል:: የዚህን የማጣራት ቃለመጠይቅ ቅጂ ማግኘት በጣም አስፈላጊ ነው:: 

 

የመታሰረ ሰጋት 

እንደ ጥገኝነት ፈላጊ ሰው በዚህ ሂደት ውስጥ በማንኛውም ጊዜ በቁጥጥር ስር ሊቆዩ ይችላሉ:: በጥገኝነት ሂደቱ ወቅት የተወሰኑ በቁጥጥር ስር ሊቆዩበት የሚችሉበ ሁኔታዎች አሉ፣ የማጣራት ቃለ መጠይቅ ከነሱ አንዱ ነው:: የመታሰረ ሰጋት ካለ እንዴት ማዘጋጀት እንደሚቻል የበለጠ መረጃ እዚህ ይገኛል https://righttoremain.org.uk/toolkit/detention/ 

መብቶችዎን ይወቁ 

የውሸት ፓስፖርት ከተጠቀሙ የጥገኝነት ጥያቄዎን ለመቀበል አያመንቱ:: የስደተኞች ስምምነት አንቀጽ 31 (the Article 31 of the Refugee Convention) ሰዎች ሀገራቸውን ለመልቀቅ የውሸት መረጃ እንዲጠቀሙ የሚያስገድድ ሁኔታ ከግምት ያስገባል:: በተለይ ሰዎች በአውሮፕላን ማረፊያው ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ስመጡ ይህን ማስታወስ በጣም አስፈላጊ ነው:: 

የጓደኛዎ፣የቤተሰብ አባል ወይም የRefugee Info Bus ፌስቡክ ገፀ እርስዎ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም እንደደረሱ ይወቁ:: ከተያዙ ወይም ከታሰሩና ከ48 ሰዓቶች በላይ ከቆዩ ማንቂያ በማሰማት ለእርስዎ ህጋዊ እርዳታን ለማግኘት ሊሞክሩ ይችላሉ:: 

ጠቃሚ ሲልከ ቁጥሮች 

Migrant Help ሲልከ ቁጥር ይያዙ ጠቃሚ ነው በUK ሀገር ውስጥ ሊረዱዎት ይችላሉ:: 

Migrant Help: 0808 8000 630 / ah@migranthelpuk.org 

This page is run by the UK registered charity, Refugee Info Bus - for more info on our work, check out our website. 

PO BOX:  Po Box 28652, Edinburgh, EH4 9EX

Registered UK Charity Number: 1168538

  • Facebook
  • Twitter
  • Instagram