በUK ሀገር ወደብ ላይ ተገኝቻለሁ፤የእኔ አማራጮች ምንድ ናቸው? 

የጥገኝነት ማመሌከቻ ሂደት በወደብ ላይ 

ፓስፖርት ወይም ህጋዊ የመጓጓዣ ሰነዶች ከሌለዎት የእርስዎ ብቸኛ አማራጭ ጥገኝነት መጠየቅ ነው:: በተቻለ ፍጥነት ጥገኝነት መጠየቅ ለአርሶ ጠቃሚ ነው:: ወደ ወደቡ ሲደርሱ እዚያ ውስጥ ለሚሠራ ሠራተኛ ያሳውቁ:: የጭነት መኪና ጀርባ ውስጥ ከሆኑ እና ወደ ፖርት ውስጥ ከገቡ በጣም ጥሩው እርምጃ ወደ ፖሊስ መደወል ነው:: ጥገኝነት መጠየቅ እንደሚያስፈልግዎ ለሠራተኛው ያስረዱ:: ይህን ለማድረግ መብት አለዎት:: የጥገኝነት ማጣሪያ ቃለ መጠይቅ ከኢሚግሬሽን ወኪል ጋር ወደብ ላይ ያደርጋሉ :: ቃለ-መጠይቁ እስከ አራት ሰአት ሊወስድ ይችላል:: 

በእርጋታ ለመቆየት ይሞክሩ፣ ድምጽዎን ከፍ አያድርጉ፣ ለሠራተኞቹ ኪበር ይስጧቸው፣ የምታደርጉት ነገር ሁሉ ሕጋዊ ነው:: 

ከHome Office የመጣ ጠያቂ በቃለ-መጠይቁ ወቅት በምርመራ ቃለ መጠይቅ ላይ ማስታወሻ ይይዛል:: የዚህን የማጣራት ቃለመጠይቅ ቅጂ ማግኘት በጣም አስፈላጊ ነው:: 

Right to Remain በምርመራ ቃለ መጠይቅ ላይ ምን እንደሚያደርግ ጥሩ ምክር ይሰጣልhttps://righttoremain.org.uk/toolkit/screening/ በተለያየ ቋንቋ ይገኛል. በዚህ የማጣቀሻ ቃለ-መጠይቅ እና ከሆም ኦፊስ (Home Office) ጋር ወደ ፊት የሚያረጉት ውይይት ተመሳሳይ መሆን አለበት:: 

ጥገኝነት ለመጠየቅ ያቀረቡት ጥያቄ ወደብ ላይ ውድቅ ሊደረግ የሚችለው 

-  ከዚህ ቀደም ከእንግሊዝ እንዲወጡ / በግዳጅ እንዲወጡ ተደርጎ ከሆነ

-  ከ 500 ፓውንድ በላይ የ NHS እዳ ካለቦዎት

-  ኢሚግሬሽን ባለሥልጣን ለመግባት ያለዎትን መብት ለመደገፍ በቂ ማስረጃ አላቀረቡም ብሎ ካመነ 

ውድቅ የተደረገውን መግቢያ ይግባኝ ማለት 

መብቶችዎን ይወቁ: የውሸት ፓስፖርት ከተጠቀሙ የጥገኝነት ጥያቄዎን ለመቀበል አያመንቱ:: የስደተኞች ስምምነት አንቀጽ 31 (the Article 31 of the Refugee Convention) ሰዎች ሀገራቸውን ለመልቀቅ የውሸት መረጃ እንዲጠቀሙ የሚያስገድድ ሁኔታ ከግምት ያስገባል:: በተለይ ሰዎች በአውሮፕላን ማረፊያው ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ስመጡ ይህን ማስታወስ በጣም አስፈላጊ ነው:: 

ጠቃሚ ሲልከ ቁጥሮች 

Migrant Help ሲልከ ቁጥር ይያዙ ጠቃሚ ነው በUK ሀገር ውስጥ ሊረዱዎት ይችላሉ::

 

Migrant Help: 0808 8000 630 / ah@migranthelpuk.org 

የጓደኛዎ፣የቤተሰብ አባል ወይም የRefugee Info Bus ፌስቡክ ገፀ እርስዎ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም እንደደረሱ ይወቁ:: ከተያዙ ወይም ከታሰሩና ከ48 ሰዓቶች በላይ ከቆዩ ማንቂያ በማሰማት ለእርስዎ ህጋዊ እርዳታን ለማግኘት ሊሞክሩ ይችላሉ:: 

መልካም እድል! ጥንካሬ እና መልካም ምኞቶችን ይደረሶት ለደህንነትዎ አስተማማኝ ቦታ አግኝቷል ብለን ተስፋ እናደርጋለን:: 

This page is run by the UK registered charity, Refugee Info Bus - for more info on our work, check out our website. 

PO BOX:  Po Box 28652, Edinburgh, EH4 9EX

Registered UK Charity Number: 1168538

  • Facebook
  • Twitter
  • Instagram