አዲስ አገር ውስጥ ከገባሁ በኋላ ቤተሰቦቼ ሊገናኙኝ ይችላሉ ? 

ዳብሊን III የቤተሰብን መልሶ ማገናኘት 

ከቤተሰብዎ ተለያይቶ መሄድ አስቸጋሪ እና ልብ የሚነካ ነው::Refugee Info Bus ይህን እውነታ በመረዳት ከቤተሰብዎ ጋር እንደገና መገናኘትን በተመለከተ ይህን የመረጃ ሰነድ አዘጋጅቷል:: 

ቤተሰብን መልሶ ለማገናኘት መጠየቅ የሚችሉት ይህን ብቻ አይደለም:: ኢባኮ Refugee Info Bus በተለያዩ አገሮች ቤተሰብን መልሶ ማገናኘት ላይ ያዘጋጀውን ሰነድ አና የቤተሰብ ቪዛዎች በተመለከተ ከተለያዩ ምንጮች መረጃዎችን ይመልከቱ:: 

ይህ የመረጃ ሰነድ በዳብሊን ሀገር ውስጥ ለሚገኙ እና በዳብሊን 3 አገር ውስጥ ያለ የቤተሰብ አባል ላላቸው ነው:: የደብሊን III አገሮች ኦስትሪያ፣ ቤልጂየም፣ ቡልጋሪያ፣ ክሮኤሺያ፣ ቆጵሮስ፣ ቼክ ሪፖብሊክ፣ ዴንማርክ፣ ኤስቶኒያ፣ ፊንላንድ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ኔዘርላንድ፣ ሃንጋሪ፣ አይስላንድ፣ አየርላንድ፣ ጣሊያን፣ ላቲቪያ፣ ሊቼንስታይን፣ ሊቱዌኒያ፣ ሉክሰምበርግ፣ ማልታ፣ ኖርዌይ፣ ፖላንድ፣ ፖርቱጋል፣ ሩማኒያ፣ ስሎቫኪያ፣ ስሎቬንያ፣ ስፔን፣ ስዊድን፣ ስዊዘርላንድ እና ዩናይትድ ኪንግደም ናቸው:: 

እርስዎ እና የቤተሰብዎ አባል በዳብሊን III አገር ውስጥ በህጋዊነት መኖር አለባቸው (ስደተኛ፣ የስደተኞች ጥበቃ፣ ጥገኝነት ጠያቂ ወይም ዜግነት ሊኖራቸው ይገባል) በዳብሊን III ውስጥ የቤተሰብ መልሶ ማገናኘት ጥያቄን መጠየቅ አለባቸው:: 

በዲብሊን III አገር ውስጥ ለጥገኝነት ወይም ለሌላ የአለም አቀፍ ጥበቃ በሶስት ወራት ውስጥ ለቤተሰብ መልሶ ማገናኘት ማመልከት ይኖርብዎታል:: 

ለዳብሊን III ከ ቤተሰብዎ ጋር መልሶ ማገናኘትን ለመጠየቅ መክፈል የለብዎትም:: ለትርጉም ሊያሰከፍሉ ይችላሉ፤ ሰነዶችን ለመላክ እና በአንዳንድ ሃገራት የዲኤንኤ ምርመራ ማድረግ ሊያስፈልግዎት ይችላል:: 

በአጠቃላይ እስከ 11 ወራት ድረስ በዲብሊን III ውስጥ ከቤተሰብ አባል ጋር አንድ መሆን አለበት. ከዚህ የበለጠ ጊዜ ሊወስድም ይችላል:: 

በዳብሊን III ሥር የቤተሰብን መልሶ ማገናኘት መጠየቅ የሚችሉት ፡

  1. ባለትዳሮች፣ ያለ ህግ ተጋቢዎች ፣ጥንድ (civil-union paarter or common law spouse)

  2. ልጆቻችሁ

  3. ያላገቡት ልጆች እድሜያቸው ከ18 በታች ከሆኑ፣ ወላጆችዎ፣ ወንድሞ፣ እህቶ፣ (የማደጎ ወንድሞችንና እህቶችን ጨምሮ)፣ አዋቂ አጎቶች፣ አክቶች ወይም አያቶች

  4. ጥገኛ የቤተሰብ አባላት

  5. በተገቢው የህግ አንቀጽ ስር የለሉ ሌሎች የቤተሰብ አባላት 

 

  1. ባለትዳሮች፣ያለ ህግ ተጋቢዎች፣ጥንድ (civil-union partner or common law spouse)

 

ባለትዳር ከሆኑ ውስጥ ወይም በዲብሊን III አገር ውስጥ በህጋዊነት ለሁለት ዓመት ከ ጥንድ ጋር በቋሚነት አብሮ ኖሮ ከሆነ ለቤተሰብ መልሶ ማገናኘት ማመልከት ይችላሉ :: 

ከትዳር አጋሮ፣ የህግ የትዳር ጓደኛዎ ጋር ያለዎት ግንኙነት ከሃገርዎ ለቀው ከመውጣትዎ በፊት መሆን ይኖርበታል:: ደብሊን III ሀገሮች ከአንድ በላይ ሚስት ወይም ጥንድ መልሶ ማገናኘት አይችሉም:: 

እርስዎ እና የትዳር ጓደኛዎ / ባልደረባዎ በድጋሚ እንዲገናኙ በዲብሊን ውስጥ ያለውን የጥገኝነት ጥያቄ ለሚያቀርቡ ባለስልጣናት በጽሁፍ ማሳወቅ አለበት:: 

 

  2. ልጆቻችሁ

 

በዲብሊን III አገር የሚኖር ልጅ ካለዎት ወይም በዳብሊን ሀገር ውስጥ በህጋዊነት የሚኖር ህጻን ልጅ ካለዎት ከእሱ ጋር መልሶ ማገናኘት ይችላሉ:: 

ቤተሰብን መልሶ ማገናኘት የሚያመለክቱት ልጅ ዕድሜያቸው ከ 18 ዓመት በታች መሆን አለባቸው:: 

ለቤተሰብ መልሶ ማገናኘት የሚያመለክቱት ለጀ ነፃ መሆን አለበት (ለምሳሌ ያላገቡ ወይም የራሳቸው ልጆች የሌላቸው):: 

እርስዎ እና ቤተሰብዎ በዳብሊንIII ማገናኘት በሚፈልጉበት አገር ውስጥ የጥገኝነት ጥያቄዎትን ለሚቀበሉት ባለስልጣናት በጽሁፍ ማሳወቅ አለባቸው:: 

 

 3. ብቻቸውን ለሆኑ ህፃናት 

ህፃን ከሆኑ አና እንደገና ለመገናኘት ከፈለጉ የሚከተሉትን ይጠበቅባቸዋል ፡ 

● ያለ ቤተሰብዎ እየተጓዙ ከሆነ ወይም ከቤተሰብዎ ተለያይቴ ከሆነ 

● ከ 18 እመት በታች ከሆነ ዕድሜዎ ከ 18 ዓመት በታች መሆኑን ማረጋገጥ መቻል አለብዎት:: ከ 18 ዓመት በላይ ከሆነ እና ሰነዶች ከሌሉት ይህ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል:: በስቴቱ የእድሜ ማረጋገጫ ሊያደርጓቸው ይችላል:: 

ከወላጆች፣ ወንድሞች እና እህቶች ጋር መልሶ ለመገናኘት መጠየቅ ይችላሉ. እንዲሁም እነሱን ሲቀላቀሉ እርስዎን እንደሚንከባከቧቸው ማረጋገጥ ከቻሉ ቤተሰብን መልሶ ማገናኘት አዋቂዎች ፡፣ አጎቶች፣ አክስቶች ወይም አያቶች ሊያጠቃሊለ ይችላሉ:: 

 

4. ጥገኞች 

ጥገኛ የሆነ ሰው እንክብካቤ ሊደረግለት የሚገባው ሰው ነው::

ወላጅ፣ ልጅ (ከ 18 ዓመት በታች መሆን የለባቸውም)፣ ወንድም ወይም እኅት በእርስዎ ላይ ጥገኛ ከሆኑ እርስዎ ቤተሰብን መልሶ ማገናኘት ይችላሉ:: 

የቤተሰብ ትስስርዎ ከአገርዎ ከመውጣትዎ በፊት መሆን አለበት. 

ጥገኛም ከሚከተሉት ውስጥ አንዱ መሆን አለበት

 ሀ. ነፍሰ ጡር

 ለ. አዲስ የተወለደ ልጅ

 ሐ. አረጋውያን

 መ. በጠና የሚታመመ 

ይህ በተለምዶ የሚከሰት ለረዥም ጊዜ ሕመም ወይም ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ሕመም (ለምሳሌ ካንሰር) ማለት ነው::

 ሠ. ወይም ከባድ የአካል ጉዳት አለበት 

የቤተሰብ አባላት እንደገና እንዲገናኙ ድጋፍ መስጠት እንዲችሉ ይህም ማለት ጥገኛውን ከኢነሱ ጋር ኢንግሊዝ አገር ንዲኖር ለመርዳት የሚያስችል በቂ ገንዘብ ማግኘት አለባቸው ማለት ነው:: 

 

5. ሐጉ ውስጥ የለሉ ሌሎች የቤተሰብ አባላት

 

አልፎ አልፎ በሌሎች አማራጮች እንደገና ለመገናኘት ብቁ ያልሆኑ ሌሎች የቤተሰብ አባላት በተለየ ሐገ አማካይነት ማመልከት ይችላሉ:: ይህ በጣም ያልተለመደ እና አብዛኛውን ጊዜ የቤተሰብ አባላት ጥገኛ ከሆኑ እና እንደገና ለመገናኘት ሰብአዊ ምክንያት ካላቸው ብቻ ነው የሚሰጡት:: 

This page is run by the UK registered charity, Refugee Info Bus - for more info on our work, check out our website. 

PO BOX:  Po Box 28652, Edinburgh, EH4 9EX

Registered UK Charity Number: 1168538

  • Facebook
  • Twitter
  • Instagram